በደረሰን ዘገባ መሰረት የሸራሮ ከተማ መስተዳድር በከተማዋ የሚገኘው የፖሊስ ጽ/ቤት የተሟላ ውስጣዊ ቁሳቁስ
ስለሌለው የከተማዋ ኗሪ ህዝብ የፖሊስ አገልግሎት ማግኘት ከፈለገ ቅድሚያ ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ግዥ የሚውል
ገንዘብ ማዋጣት እንዳለበት በማመንና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔ በማሳለፍ የጀመረው እንቅስቃሴ በህዝቡ ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።
የከተማዋ የመስተዳድር አካላት የከተማዋን ኗሪ ህዝብ በመሰብሰብ ገንዘብ እንዲያዋጣ በጠየቁበት ጊዜ ህዝቡ ፤ በመንግስት በጀት ለሚተዳደር መ/ቤት ገንዘብ ማዋጣት አይጠበቅብንም
፥ ለዚሁ መስሪያቤት የሚመደበው አመታዊ በጀት የት ገባ ? እየተከተላችሁት ያለ አሰራር ዝርፊያን እንጂ ልማትን የሚያጠናክር ስላልሆነ
ዝርፊያን እናወግዛለን በማለት ተቃውመውን ገልጻል።
መንግስት በሰበብ አስባቡ ህዝቡን መበዝበዝ አግባብነት የለውም ። በመለስ ፋውንዴሽን ስም እንድናዋጣ እየተጠየቅን
ያለው ገንዘብም ቢሆን በመሰረቱ ተቀባይነት የለውም በማለት የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል።