Thursday, August 29, 2013

በመከላከያ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የሰባት ዓመት ኮንትራት ውል የማስፈረምና የማደስ ተግባር በሰራዊቱ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የሰራዊቱ አዛዦች ውጥረት ውስጥ ገብተዋል።




በተለያዩ ግምባሮችን ተሰማርተው የሚገኙ የኢህ አዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል በፌርማቸው ኣንዲያረጋግጡ ቢጠይቁም ፈቃደኛ ሆነው አልተገኙም ። በሁኔታው የተደናገጡ የሰራዊቱ አዛዦች ኮንትራቱን የፈረመ ወታደር በሰላም አስከባሪ ሃይል ወደ ዳርፉር ይላካል ፥ የርቀት ትምህርት እድል ይሰጠዋል፥ የሞያ ስልጠና ቅድሚያ እንዲያገኝ ይደረጋል ወዘተ በሚል የማይተገበር መደለያ በማደናገር ለማታለል እየሞከሩ መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወታደሮች በውትድርና ሞያ እንዲቀጥሉ በኢህአዴግ ስርዓት እየተደረገባቸው ያለን ጫና በመቃወም ክፍላቸውን ጥለው በመጥፋት ላይ ናቸው ። በአማካይ ሲታይ ከአንድ ሃይል ከ 22 እስከ 23 ወታደሮች ኮንትራቱን የማደስ ውል በመቃወም እንደጠፉ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።