የኢህአዴግ ስርዓት ናሪነታቸው በዓዲ-ዓርቃይ ወረዳ በሆኑ ዜጎች ላይ የአከባቢው የመንግስት የመስተዳድር
አካላትን በመጠቀም የተለያየ በደል እያደረሰ ነው። በደል ከደረሰባቸው የከባቢው ኗሪዎች መካከል አንዱ አቶ አዲሱ/አለማየሁ ሶራ/
ሲሆን በደረሰበት ግፍ ተማርሮ ወደ በርሃ በመውጣት የኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም ነፍጥ አንስቶ ከስርዓቱ የመስተዳድር አካላት ጋር
ፊት ለፊት መግጠም ጀምሯል።
የኢህአዴግ ስርዓት አቶ አዲሱን አድኖ ለመግደል በርካታ የስርዓቱ ታጣቂዎችን በማሰማራት ባደረገው አሰሳና
የቶክስ ልውውጥ አራት የፖሊስ አባላት ሲገደሉ በርካታ ቆስለዋል። በፖሊስ ሲታደን የነበረው አቶ አዲሱም ለረዥም ሰዓታት ከተዋጋ
ብሁዋላ በመጨረሻ እራሱን ማጥፋቱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
በፖሊስና በህዝብ መካከል የሚደረጉ ግጭቶች በአማራ ክልል ብቻ የሚታይ ሳይሆን በሁሉም የሃገሪቱ አከባቢዎች
ባጠቃላይ እየተቀጣጠለ ያለ ህዝባዊ ተቃውሞ መሆኑን የሚታወቅ ነው።