Tuesday, August 27, 2013

ከተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ወደ ሑመራና አከባቢዋ የሚሄዱ የቀን ሰራተኞች ዘርንና አከባቢን መሰረት ባደረገ ልዩነት ሲጋጩ ይታያል።




በማይካድራ አከባቢ በእርሻ ስራ ተሰማርተው በመስራት ላይ በሚገኙ የቀን ሰራተኞች መካከል በተደጋጋሚ በሚፈጠር ዘርንና አከባቢን መሰረት ያደረገ ግጭት ሦስት ሰራተኞች በጩቤ ተወግተው በመጥረቢያ ተደብድበው የሞቱ ሲሆን ሌሎች ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሰራተኞች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በአከባቢው በሚገኘው ሆስፒታል በህክምና ላይ ናቸው።
ግጭቱን ለማቆም በመንግስት የተወሰደ እርምጃ የለም።የአከባቢው የመስተዳድር አካል ግጭቱን ለመፍታት አለመንቀሳቀሱን ግጭቱን በማቀጣጠል የስርዓቱ እጅ እንዳለበት ያመለክታል።
ይህ በእንዲህ እያለ በሑመራ በኩል ወደ ሱዳን በመጓዝ ላይ የነበሩ 45 ሶማሊያዊያን ነሃሴ 17,2005 ዓ/ም በኢህአዴግ ታጣቂዎች ተይዘው ሑመራ በሚገኘው እስር ቤት እንዲገቡ ከተደረገ ብሁዋላ ከባድ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።