በደረሰን ዘገባ መሰረት የወረዳዋ ህዝብ በ 2000 ዓ/ም የኤሌክትሪክ መስመር እንዲዘረጋለት 100 ሚልዮን
ብር እንዲዋጣ ያደረገ ሲሆን በወቅቱ የነበረው የወረዳዋ መስተዳድር ለማስመሰል የኤሌክትሪክ ምሶሶዎችን መትከል ጀምሮ ብዙ ሳይሄድ
በመሃል እንዲቃረጥ ተደርጓል።
የወረዳዋ ኗሪ ህዝብ ነሃሴ 4,2005 ዓ/ም ባካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የተዋጣውን ገንዘብ ለተፈለገው ዓላማ
ሳይውል 6 ዓመታት ተቆጠረ። ገንዘብ ለህዝቡ ይመለስለት በማለት ጠይቋል።
የዞኑ መስተዳድር ስለተዋጣው ገንዘብ በመተመለከተ እኛን የሚመለከት አይደለም ያኔ በቦታው ለነበሩ ገንዘቡን
ለተረከቡ የመስተዳድር አካላት መቅረብ የሚገባ ጥያቄ ነው በማለት ከአንድ ህዝብን እወክላለሁ የሚል የመንግስት አካል የማይጠበቅ
ምላሽ መስጠቱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።