ኢፍትሃዊ በሆነው የግብር አከፋፈል የተማረሩ የከተማዋ ኗሪዎች ነሃሴ 5,2005 ዓ/ም ለዞኑ አስተዳደር
አቶ ሚኪኤለ አብረሃ ቅሬታቸውን ለመግለጽ ቢሄዱም አስተዳዳሪው የህዝቡን ቅሬታ በማድመጥ መፍትሄ እንዳልሰጣው ኗሪዎቹ ይናገራሉ።
ወደ አስተዳደሩ ከሄዱት የከተማዋ ኗሪዎች መካከል በከተማዋ ሆቴል ያላቸ ቄስ ግደይ የተባሉ ኗሪ ፤ መንግስት
በሚከተለው ብልሹ አሰራርና በሚጭንብን ከፍተኛ ግብር አገራችን ጥለን እንድንሰደድ እየተደረገ ነው ፥ ካሁን ብሁዋላ የምጠብቀው ነገር
የለም እንዲህ ዓይነቱ ብልሹ አሰራር አንድ መፍትሄ ካልተበጀለት ሰው እየተሰደደ ከተማዋ ዎና ትሆናለች ሲሉ በስሜት መናገራቸውን
ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።