ባለፈው ዓመት ነሃሴ 14,2004 ዓ/ም በኢህአዴግ መንግስት በይፋ የተነገረው የመለስ ዜናዊ ሞትን ተከትሎ
የኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ ማዘኑን በመግለጽ በተደጋጋሚ ሲካሄድ የነበረው የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እንዳይበቃ በመላ ሃገሪቱ በገጠርም ሆነ
በከተማ ኗሪው ህዝብን የመለስ ዜናዊ አንደኛ የሙት ዓመትን እንዲያከብር ሲካሄድ የቆየ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ስላላገኘ
የኢህአዴግ መንግስት የፌደራል ፖሊስ ፤ መደበኛ ፖሊስና የሚሊሽያን ሃይል በየአከባቢው በማሰማራት ህዝቡን በማስገደድ ወደ አደባባይ
እንዲወጣ ማድረጉን ከሁሉም የሃገሪቱ አከባቢዎች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት የኢህአዴግ ስርዓት የመለስ ዜናዊ ሞትን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል እንደ አንድ ትልቅ
አጀንዳ በመያዝ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም እየተጠቀመበት ይገኛል ። ድፍን አንድ ዓመት ሙሉ መለስ ዜናዊ የሰራውንና ያልሰራውን
ታሪክ በመደርደር ሲካሄድ በቆየውና እየተካሄደ ባለው ርካሽ ፕሮፖጋንዳ የተቆጣው የኢትዮጵያ ህዝብ የመለስ ዜናዊ የሙት ዓመትን ለማክበር
ወደ አደባባይ እንድንወጣ አንገደድም ። በዚች ሃገር ሃቀኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን እንዲሆን በተካሄደው ትግል በ 10 ሽዎች
የሚቆጠሩ ዜጎች ውድ ህይወታቸውን ከፍለዋል ። ክብር መስጠት ካለብን ለነዚህ ሰማእታት ነው ክበር መስጠት የሚገባን ሲሉ ተቃውመውን
ገልጻል።
መለስ በስልጣን ላይ በቆየባቸው ያለፉት 21 ዓመታት ህወሓት በትጥቅ ትግሉ ሲታገልለት የነበረ ዓላማና ለህዝቡ
የገባለትን ቃል ሙሉ ለሙሉ በመካድ የጥቂት ሰዎችን ጥቅም ለማረጋገጥ ሲሰራ የቆየ በመሆኑ ሊኮነን እንጂ ለእንዲህ ዓይነቱን ኢዲሞክራሲያዊ
መሪ ክብርና ሞገስ መስጠት አይገባም በማለት በትግራይ በግልጽ የተቃወሙ ሰዎች ነሃሴ 14,2005 ዓ/ም በፌድራል ፖሊስ አሸባሪዎች
በሚል ተይዘው የተቀጠቀጡና ደብዛቸው የጠፋ መኖራቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።