Saturday, September 7, 2013

ከደሴ ወደ መቐለ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ነሃሴ 28,2005ዓ/ም በደረሰብት የመገልበጥ አድጋ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አስከተለ።




ከደሴ ከተማ በመነሳት ተሳፋሪዎችን ጭኖ ወደ መቐለ ከተማ በምጓዝ ላይ የነበረው አውቶብስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ በውስጡ ከነብሩ ተሳፋሪዎች መካከል 15 ወድያውኑ ህይወታቸውን ሲያጡ በሌሎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ማድረሱን ቷውቋል።
የአደጋው መንስኤ ሁለቱንም ክልሎች የሚያገናኘው የመኪና መንገድ በዝናብ ተቦርብሮ በመበላሸቱና እድሳት ስላተደረገለት ነው ሲሉ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያዎች ይናገራሉ።
በያዝነው ሳምንት አንድ የትራንስ ኢትዮጵያ ከባድ ተሽከርካሪ በዓዲ-ቐይሕ በተባለ አከባቢ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ መዘገባችን የሚታወስ ነው።