ኢህአዴግ በመላ አገሪቱ በተለይም በትላልቅ ከተሞች የሚኖር ህዝብን በማስፈራራት ለማታለል እንደሚሞክረው
ሁሉ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማም በህዝቡ መካከል አሸባሪዎች እንደገቡ ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተላላኪ አሸባሪዎች እንደሆኑ አድርጎ በማቅረብና
በአሁኑ ጊዜ በህዝቡ ላይ ከፈተኛ የሸባሪዎች አደጋ እደተጋረጠ በማስመሰል እራሱ ኢህአዴግ የፈበረካቸው የፈጠራ ፊልሞችን ህዝቡን
በማስገደድ እንዲመለከት በማደረግ ለማሳመን የሞከረ ቢሆንም ሊሳካለት እንዳልቻለ ቷውቋል።
ህዝቡ ከዚህ ቀደም ጃሃዳዊ ሃረካትና አኬልዴማ በሚሉ ርእሶች በመንግስት የቀረቡትን አሳማኝ ያልሆኑ ድራማዎችን
በመመልከቱና የኢህአዴግን ባህሪ በሚገባ በመገንዘቡ አሁን በጸረ-ህዝቡ ስርዓት እየተደረገ ያለውን አሸባሪዎች ገቡ የሚል ቅስቀሳ
መቋወሙን ቷውቋል።