Saturday, September 7, 2013

ኗሪነታቸው በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የሆኑ ነጋዴዎች መንግስት ከምናገኘው ገቢ ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር ጫነብን ይላሉ።




እንደ ተበዳይ ነጋዴዎች አባባል ከሆነ መንግስት ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ እንዳስገደዳቸውና ከስርዓቱ ካድሬዎች ጋር ትስስር ያላቸው ነጋዴዎችን መክፈል ከሚገባቸው በታች ዝቅተኛ ግብር እንዲከፍሉ ሲደረግ ከስርዓቱ ካድሪዎች ጋር ህገ ውጥ ግንኝነት በማያድርጉ ነጋዴዎች ላይ ደግሞ መክፈል ከሚገባቸው በላይ ከፈተኛ ግብር እንዲከፍሉ ይደረጋል።
ከገቢያችን በላይ ከፍተኛ ግብር ተጫነብን የሚሉ ነጋዴዎች ከመሃከላቸው ሰዎችን በመወከል እስከ ክልል ድረስ በመሄድ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም አድማጭ እንዳላገኙ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ ከተወሰነባቸው ነጋዴዎች መካከል በከተማዋ ኮንጎ ጫማ ቤት ያላቸው አቶ ፍስሃ በርሀ 40 ሽህ ብር እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው ሲሆን በተመሳሳይ አቶ ጸጋይ ገ/ማሪያም በከተማ ግሮሰሪ ያላቸው ሆኖ 190 ሽህ ብር እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።