Thursday, September 12, 2013

የመቐለ ከተማ መስተዳድር የዓይናለም አከባቢ ኗሪዎችን በማስነሳት ቦታው ለባለ ሃብቶች በሊዝ እንዲሸጥ ወሰነ።



በመቐለ ከተማ በተለምዶ ዓይናለም እየተባለ በሚጠራው ልዩ ቦታ በባለሃብቶች ስለተመረጠና በከተማዋ መስተዳድር በሊዝ እንዲሸጥ ስለተወሰነ በአከባቢው ሲኖሩ የነበሩ ዜጎች 90 ካሬ ሜትር ተለዋጭ መሬት በነፍሰወከፍ እንደሚሰጣቸው አውቀው የግል ንብረታቸውን በመሸከፍ ተሎ አከባቢውን እንዲለቁ ፥ በተባለው ጊዜ የማይነሳ ካለ መንግስት ዶዘር በማሰማራት ማፍረስ እንደሚጀምር መመሪያ መስጠቱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
      በከተማዋ መስተዳድር የመንግስት ባለስልጣናት ፤ የአከባቢው ኗሪዎችን ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አከባቢ ሆን ብለው በማፈናቀል መሬት በሊዝ በመሸጥ አለአግባብ ሃብት ለማካበት እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በተወሰነ ውሳኔ መሆኑ የተረዱ የውሳኔው ሰለባ የሆኑ ኗሪዎች ለዓመታት ጥረን ግረን የገነባነውን ቤት ጥለን አንወጣም በማለት በአድን ድምጽ ተቃውማቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።