የትግራይ ክልል ርእሰ ከተማ የሆነችው መቐለ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ
መጥቶ በአሁኑ ጊዜ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል ። የክልሉ መስተዳድር በተለያየ ጊዜ የከተማዋን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር
ለመፍታት ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ቢናገርም ችግሩ እየተባባሰ ሲሄድ እንጁ ሲቃለል አልታየም።
ችግሩ ሁሉንም ክፍለ ከተሞችን የሚያካልል ሆኖ በተለይም በዓይደር ፤ በዓዲ ሽንድሑ ፤ በ 03 ና 18 ቀበሌዎች
እጅግ የከፋ ነው ። የአከባቢው ኗሪ ህዝብ ካለፉት ሦስት ወራት ጀምሮ ጥራት የሌለው የጉድጓድ ውሃ ለመጠቀም መገደዱን ከቦታው የደረሰን
ዘገባ ያስረዳል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በዓብይ ዓዲ ከተማ በሚታየው የንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርና የመብራት በተደጋጋሚ
መቆራረጥ የከተማዋ ኗሪዎች እለታዊ ኑራቸውን በአግባቡ መምራት መቸገራቸውን ገልጸዋል።