በደረሰን ዘገባ መሰረት እነዚህ ከተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች በመምጣት በሑመራ ከተማና አከባቢዋ በጉልበትና
በሸቀጣ ሸቀጥ ስራ የተሰማሩ ዜጎችን የኢህአዴግ ስርዓት በዘርና በአከባቢ በመከፋፈል በመሃከላቸው መተማመን እንዳይኖርና እርስ በራሳቸው
እንዲጋጩ በማድረግ ሰራተኞቹ ዋስትና አጥተው የጀመሩትን ስራ በመተው ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ወደየአከባቢያቸው ለመመለስ ተገደዋል።
በተፈጠረው ችግር ምክንያት በአከባቢው በእርሻ ስራ የተሰማሩ ባለሃብቶች ሰራተኛ ማግኘት ስላልቻሉ እርሻቸው
በአረም ተውጦ ለኪሳራ መዳረጋቸውን ይገልጻሉ።
በስጋት ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት በዜጎች መካከል መግባባትና መተባበር እንዳይኖር በማድረግ የስልጣን
እድሜውን ማራዘም እንደ አንድ ስልት እየተጠቀመበት የመጣ መሆኑ የሚታወቅ ነው።