Thursday, October 10, 2013

በጤና አገልግሎት አለመኖር ምክንያት በአስገደ ጽምብላ ወረዳ በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን እያጡ ነው፣



በሰሜን ምዕራብ ዞን ፤ በአስገደ ጽምብላ ወረዳ ወባን ለመቆጣጠር በአከባቢው መስተዳድር የተደረገ ምንም ዓይነት ቅደመ ዝግጅት ባለመኖሩ ምክንያት በወረዳዋ አብዛኛው አከባቢ በወባ በሽታ በመጠቃቱ በርካታ የአከባቢው ኗሪዎች ህይወታቸውን እያጡ ነው፣ በተለይም በዕዳጋ ሕብረት ፤ ዓዲ ራህዋና ዓዲ መሐመዳይ አከባቢ ወረርሽኙ በመባባሱ በኗሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው፣
የአከባቢው የመስተዳድር አካላት መስከረም 16/2006 ዓ/ም ኗሪውን ህዝብ በመሰብሰብ ጾታና እድሜ ሳይለይ እየፈጀ ያለውን ወረርሽኝ እንደ አጀንዳ መያዝ ሲገባቸው ሌላ የራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ በማንሳታቸው ህብረተሰቡ ለችግራችን መፍትሄ የማትሰጡ ከሆነ ከናንተ ጋር የሚያገናኝ የለንም በማለት ሰብሰባውን ረግጦ ወጥታል፣