በደረሰን ዘገባ መሰረት በአማራ ክልል ፤ በመተማ ወረዳ ፤ ሽኸዲ ከተማ አንድ የፖሊስ አባል መስከረም
4,2006 ዓ/ም ገንዘብ እዲሰጡት ጠይቃቸው ፈቃደኛ ስላልሆኑ ሁለቱንም ወጣቶች ጥይት በመተኮስ ገድላቸዋል፣ ወጣቶቹ ወደ አከባቢው
የሄዱት ስራ ፍለጋ ሲሆን ሁለትም የክልሉ ኗሪዎች ናቸው፣
ሟቸቹ በለጠ ቸኮልና ቸርነት አድማሱ የተባሉ ሲሆኑ የብሄረ አማራና የብሄረ አገው ተወላጆ ናቸው፣ የፖሊስ
አባሉ እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር አልዋለም ፣ ኗሪነታቸው በአከባቢው ያልሆነ ስራ ፍለጋ የሄዱ ዜጎች በሁኔታው ተደናግጠው በስጋት
ውስጥ መግባታቸውን የደረሰን ዘግባ ጨምሮ ያስረዳል፣