በሰቲት ሑመራ ከተማ በከተማዋ መስተዳድር የተጠራ ለነባር የህወሓት ታጋዮችን ብቻ የሚመለከት ስብሰባ መስከረም
27,2006 ዓ/ም የተደረገ ሲሆን መንግስት ልዩ ቱክረት በመስጠት ታጋዮችን ለመርዳት መነሳቱንና ለአሰራር ያመች ዘንድ መደራጀት
እንደሚገባቸው በመድረኩ አመራሮች የቀረበ ፕሮፖጋንዳ በተሰብሳቢዎቹ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ለመረዳት ተችሏል፣
ነባር
ታጋዮቹ መንግስት እያቀረበው ያለውን ሃሳብ ላለፉት 22 ዓመታት በተደጋጋሚ የተነገረ ግን ተግባራዊ ሲሆን አልታየም፣ ዛሬም ሆነ
ነገ በመንግስት ቁጥጥር ስር ለመደራጀት የሚፈልግ ነባር ታጋይ ሆነ ህዝብ የለም በማለት መቃወማቸውን ቷውቋል፣