በመረጃው መሰረት በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ የዕጉብ ኬላ
ቀበሌ ነዋሪዎች በህጋዊ መንገድ በተሰጣቸው መሬት እንደሸቀጣሸቀጥ ዓይነት ድርጅቶችን ከፍተው ኑሮአቸውን ሲመሩበት የነበሩ ቤታቸው
ከሚያዝያ 29 ጀምሮ እስከ ግንቦት 7 2006 ዓ/ም በስርዓቱ ተላላኪዎች የፈረሰ ሲሆን ቤታቸው ከፈረሰባቸው ወገኖቻችን መካከልም ።-
Ø አቶ አማረ መኮነን 2 ክፍል ቤት
Ø አቶ ንጉሴ ብርሃነ 2 ክፍል ቤት
Ø ቄስ በርሃን ገርህላሰ 3 ክፍል ቤት
Ø አቶ ታረቀ ታደሰ 3 ክፍል ቤት
Ø አቶ አለም ወለገብርኤል 4 ክፍል ቤት
Ø ቄስ አዳነ ታደሰ 4 ክፍል ቤት
Ø ፅዋ መኮነን
Ø አረጋይ ሰጋ
Ø አቶ ብርሃኑ መኮነን
Ø ተክላይ ወለአረጋይና ሌሎችም እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቤት በማፍረስ ከተሰማሩ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ውስጥ
ደግሞ ገብረአብዝጊ ኪዳነና ምክትሉ ተስፋዮሃንስ መሰለ እንዲሁም የስራ
ባልደረባቸው ፍታአለም ገብረማርያም ጋር በመሆን ያላአገባብ የቤቱን
ምሰሶ በመስበራቸው በርካታ የቤት ንብረት እንደተበላሸና ነዋሪዎችም ያለምንም መጠለያ በረሃ ላይ ተጥለው እየተሰቃዩ
እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።