Monday, June 23, 2014

የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማስተካከል ያዋጡት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በታለመለት ሥራ ባለመዋሉና አስተዳዳሪዎቹ አስፈላጊውን ክትትል ባለማድረጋቸው ምክንያት በመበላሸቱ ሰኔ 10/2006 ዓ.ም ስራውን ማስቆማቸው ተገለፀ፣፣



ታማኝ ምንጮቻችን ከከተማዋ እንደዘገቡት የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ለከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብለው ባዋጡት ገንዘብ እንዲሰራ ኩንትራት የያዘው የቻይና ኩባንያ ሲሆን የሚመላከታቸው የመንግስት አካላት ከኮንትራክትሩ ጋር አላስፈላጊ ግንኙነት ስላደረጉና ስራው በጥራት እንዲሰራ ክትትል ባለማደረጋቸው ምክንያት እየተበላሸ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣
    ነዋሪዎች ሰኔ10/ 2006 ዓ.ም የቻይና ኮንትራክተር መንገዱን እያበላሸብን ስለሆነ ጥራት ባለው መንገድ እንዲሰራልን ነው የምንፈልገው በማለት አስገድደው ስራውን እንዳስቆሟቸው ከገለፀ በኋላ የከተማዋ አስተዳዳሪው ልክ ናችሁ አበላሽተውታል ጥሩ አድርገን እናስተካክለዋለን ብሎ ሊያታልላቸው ቢሞክርም የሁመራ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ግን በሚሊዮናት የሚገመት ገንዘብ አውጥተን ከተማችንን አበላሻችሁት በማለት ተቃውሞአቸውን እየገለፁ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስታውቋል፣፣