ምንጮቻችን
በላኩት መረጃ መሰረት በሁመራ የሚገኙ በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ
ባለሃብቶች “እቶት” ለተባለው የመንግስት ድርጅት አንድ ባለሃብት 100 ኩንታል ካመረተ ባገኛት 100 ኩንታል ሂሳብ መሰረት መክፈል
ሲገባው የ200 ኩንታል ቀረጽ እንዲከፍሉ በማስገደድ ወደ አልተፈለገ ዕዳ እንዲገቡ እያዳረጓቸው እንዳሉ ታውቋል፣፣
በዚህ ምክንያት
እኒህ ባለሃብቶች መንግስት ላባችንን አፍስሰን የገኘነውን ምርት መልሶ አምጡት እያለን ስለሚገኝ ሰርተን ልንለወጥበትና ወገንን ልንረዳበት
በማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰን እንገኛልን ሲሉን ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣፣