በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ
ዞን በታህታይ እድያቦ ገጠሮችና በሸራሮ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከህወሃት የትጥቅ ትግል ጀምረው ካድሬዎች ሆኖው ሲያገለግሉ የቆዩ አባላት ውጤት በማያስገኘው የድርጅቱ ተደጋጋሚ
ስብሰባና ግምገማ ተሰላችተው የድርጅቱ አባልነት ይቅርብን ብለው ወጥተው ለቆዩ ወገኖች እንደገና ተመልሰው እንዲገቡ ለማድረግ ካድሬዎቹ
በጥብቅ እየለመኗቸው እንደሆነ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣፣
የህወሃት
አስተዳዳሪዎች በአካባቢው እንደ አንድ ትልቅ አጀንዳ ይዘው እየተንቀሳቀሱበት ያለው ምክንያት በገዛ ፈቃዳቸው ከህወሃት ተሰናብተው
የቆዩትን አባላትን የ2007 የምርጫ ወቅት ሳይደርስ ወደ አባልነታቸው ለመመለስ በሚል ድርጅታቹህ ለማን ጥላችሁት ነው የምትሄዱት?
ከህወሃት የሚያራርቅ ምን ምክንያት ተገኘ? ወደ ድርጅታቹህ ተመለሱ እንጂ አስፈላጊውን እገዛ እናደርግላቹሃለን እያሉ ሊያነሳስዋቸው
ቢሞክሩም ሰሚ እንዳላገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣፣
ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ ከጠየቁና ከዚህ በፊት በአባልነት ስያገለግሉ
ከቆዩት ጥቂቶቹን ለመጥቀስ።
- ወ/ሮ መድህን፤ ወ/ሮ ፅጌ ሃይለስላሴና አቶ ኪሮስ የተባሉት ነዋሪነታቸው በሸራሮ ከተማ የሆኑትን አካል
ጉዳተኞች
- አቶ ገብረመስቀል ዓንደ ከኩናማ ብሄረሰብ
- ሻለቃ ተኽላይ ገብረማርያምና እቶ ደስታ ሃይለ ነዋሪነታቸው በአዲ ሃገራይ ሲሆኑ
በተለይ ለሻለቃ ተክላይ ወደ አባልነት እንዲመለስ ጥያቄ ባቀረቡለት ሰአት እንናተ እንደማታስፈልጉኝ አስቀድሜ
ስለወጣሁኝ አሁን እንደገና የምመለስበት ምክንያት የለኝም እባካችሁ እረፍት ስጡኝ በማለት ጥያቂያቸውን እናዳልተቀበለው በስብሰባው
ተሳታፊ ከነበሩ ምንጮቻችን ለማወቅ ተችሏል፣፣