Saturday, June 28, 2014

በአ/ራፊዕ ከተማ የሚገኙ ሰራተኞች በከተማዋ አስተዳዳሪዎች የመኖሪያ 200 ብር እንዲከፍሉ መገደዳቸውና አንከፍልም ላሉት ደግሞ እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ፣፣




በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አውደራፊዕ ከተማና አከባብዋን ሰፊ የእርሻ ቦታዎች የሚሸፍን በመሆኑ ምክንያት ከተለያዩ የሃገራችን አከባቢዎች  ወደ ቦታው ለመስራት የሚገቡ ሰራተኞች “ ከቦታ ወደ ቦታ ተቀሳቅሰን ሰርተን ለመኖር ህገ-መንግስታዊ መብታችን ነው። መልኩ የቀየረ ግብር አንከፍልም “ ብለው ለተናገሩ ሰራተኞች የከተማዋ አስተዳደር፤ የፖሊስ አባላትና የምልሻ ታጣቂ አንድ ላይ በመሆን ሰራተኞችን ከተሰማሩበት የስራ መስክ እተለቀሙ እንደሆኑና እስከ አሁን ድረስም ወደ 40 የሚሆኑትን ሰራተኞች መታሰራቸው ምንጮቻችን አስረድተዋል፣፣
     የዓብደራፊዕ ከተማ ህዝብም “ ሰራተኞች ያለኛ እኛ ያለ ሰራተኞች መኖር አንችልም በጉልበቱ ሰርቶ ለሚኖር ሰው ገንዘብ ክፍል መባሉ አግባብነት የለዉም ” ማለታቸውና ለዚህ ተግባር ከተቃወሙት የአከባቢው ሽማግሌዎችና ባለ ሃብቶች መካከልም….
1.  አቶ ተፈራ ገንዘቡ
2.  አቶ ደግፈው ሓገዞም
3.  አቶ ክንደያና ሌሎችም ሲሆኑ ወደ አከባቢው ለመስራት የሄዱ ሰራተኞችም በአስተዳዳሪዎች እኩይ ተግባር ተደናግጠው ወደ ትውልድ አከባቢያቸው እየተመለሱ በመሆናቸው ምክንያት በአከባቢው የሚገኙ ባለ ሃብቶች በሰራተኞች እጦት ምክንያት ስራቸው እየተስተጓጕለ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል፣፣