Friday, June 20, 2014

በመቐለ ከተማ የቀበሌ 18 ነዋሪ የሆኑት እናት፣ልጅሽን ወደ ት.ህ.ዴ.ን ልከሻል በሚል ሰበብ ተከሰው ወደ ፍርድቤት መቅረባቸውን ምንጮቻችን ከመቐለ ከተማ አስታወቁ፣፣



በመረጃው መሰረት፣የ56 ዓመት የሆኑት እናት ታስረው ቀበሌ 16 በሚገኘው ማእከላይ ፍርድ ቤት ቀርበው ልጅሽን  ወደ ትህዴን መላክሽ አልበቃ ብሎሽ ለራስሽም የትህዴን ተባባሪ ነሽ ብለው በተጠየቁበት ግዜ ልጄ ወዴት እንደሄደ አላውቅም ድሮ ለናንተ እየተባበርናችሁ አልነበርንም አሁን ለእነሱ መተባበራችን ምን ሃጢያት አለው ልጆቻችን አይደሉም እንዴ? በማለት ደፍረው በመናገራቸው ፍርድ ቤቱ ውስጥ ሆኖ ይሰማ የነበረው ህዝብም በአነጋገራቸው እንደተደሰተ ለጉዳዩ ሲከታተሉ የነበሩ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣፣
    የህወሓት-ኢህአደግ ስርአት ንፁሃን ሰዎችን ባልሆነውና ባልተጨበጠ ጉዳይ እየከሰሰ ለራሱ በሚመቸው ጥላሸት እየቀባ ላንዱ ፀረ ህዝብ ለሌላው ደግሞ ተላላኪዎችና ደጋፊዎች እያለ እንደሚያሰቃያቸው ይታወቃል፣፣