በመረጃው መሰረት ፣የአብረሃ አፅብሃ አስተዳዳሪ የሆነው ገረንሰአ ግደይ ( አባ ሓዊ ) የዓረናን ፕሮግራም ለህዝብ ለማስተዋወቅ ከተንቀሳቀሱ
አባላት ዓንዶም ገብረስላሴና አፈወርቂ ለተባሉ ተቃዋሚዎች አስሮ ከአከባቢው ሲያባርራቸው በአብረሃ አፅብሃ የዓረና አስተባባሪ ኮሚቴ
የሆነው ቴድሮስ ሞጎስ ደግሞ እስከ አሁን በውቕሮ ከተማ ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣፣
በአባ-ሓዊ የሚታወቀው ፀረ ህዝብ የወያኔ
ኢህአዴግ ካድሬ በህዝብ ስም እየነገደ እያስተዳድርኩህ ነኝ ለሚለው ህዝብ እየበዘበዘ ከዜሮ ተነስቶ የ6 መኪኖች ባለቤት መሆኑን የአከባቢው ህዝብ እየገለፀ ይገኛል፣፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በስልጣን ላይ
ያለው ስርአት በተለይ ደግሞ ህወሓት-ማሌሊት በቅራኔ ጎራ ተከፋፍሎ
ባልተረጋጋ ሁኔታ ሆኖ በ 2007 ዓ/ም ሊያካሂደው ባሰበው የይስሙላ ምርጫ ሊወዳደሩኝ ይችላሉ በሚል ስጋት ከ200 በላይ የዓረና
አባላትን በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች አስሯቸው እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣፣