Friday, June 20, 2014

በአማራ ክልል አዊ ዞን የኮሶበር ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ 8 አመራሮች በፀረ ሙስና ኮሚሽን እንደታሰሩ ምንጮቻችን ገለፁ፣፣



በአዊ ዞን የኮሶበር ከተማ አስተዳደር መሪ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ ስምንት አመራሮች በከተማዋ የሚገኘውን 14 የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በህገ ወጥ መንገድ ጉቦ እየተቀበሉ መሸጣቸውን የተከታተለው የከተማው ማህበረሰብ ባደረገው ጥቆማ በፌድራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን አጋችነት ታስረዋል፣፣
   እነኝህ በሙስና የተጨማለቁ የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናትና ባለሙያዎች ሃላፊነት የጎደለው ህገወጥ የከተማ ቦታ ሽያጭ  በመፈፀማቸው  በተበደለው ህዝብ ጥረት ወደ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ተመጣጣኝና አስተማሪ ውሳኔ ሊሰጣቸው እንደማይችል የአከባቢው ማሕበረሰብ እየተናገረ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣