እኒህ በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮች በገዥው መንግስት
የቀረበው የምርጥ ዘር ዋጋ ካለፈው አመት በእጥፍ ስለጨመረ ገዝተው መጠቀም ባለመቻላቸው ምሬታቸውን እያሰሙ እንደሚገኙና ጭማሬ ከተደረገባቸው
ዘሮችም፤ ጤፍ ለ50 ኪሎ ግራም በ1450 ብር ፥ለ50 ኪሎ ግራም ስንዴ ደግሞ በ900 ብር ሂሳብ በቅድመ ክፍያ እንደሆነና 20
% ወለድ እንዳለው የገለፀው መረጃው አርሶ አደሮች በቀዝቃዛ አካባቢዎች የሚዘራ የድንች ዘር እንዲቀርብላቸው በተደጋጋሚ ጠይቀው
ምላሽ ባለማግኘታቸውም የተሰማቸውን ምሬት ገልፀዋል፣፣
በተመሳሳይ ዜና
በአማራ ክልል አዊ ዞን የሚገኙ የዳንግላ አዲስ ቅዳም ኮሶ በር ግምጃ ቤትና ቲሊሊ ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች ከ7 አመት በፊት ለፖለቲካ
ፍጆታ ስልጣን ላይ ባለው ስርዓት በነፃ የታደላቸው የኤክስቴሽን ግብዓት በዚህ ወር በግዴታ እንዲከፍሉ የፀጥታ ግብረሃይል ተደራጅቶ
ወደ ወረዳዎች እንደገባ ከስፍራው ምንጮቻችን አስረድተዋል፣፣
የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት በህዝብ ያላቸው ተቀባይነት ከግዜ ወደ
ጊዜ እየወረደ ስለመጣ፣በምርጫ ጊዜ ምረጡን ወይም ደግሞ በነፃ የወሰዳችሁትን ገንዘብ ይሁን ንብረት ክፈሉ ማለት የተለመደ እኩይ
ተግባራቸው መሆኑን አርሶ አደሮቹ እየተናገሩ ሲሆን፣ ይህ ተግባርም በአካባቢያቸው ብቻ ሳይሆን በመላ ሃገሪቱ እየተፈፀመ ያለ ጉዳይ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል፣፣