በስርዓቱ የወረደውን
የማስገደድ ፕሮግራም ሊከፍሉ ፍቃደኛ ያልሆኑት አርሶ አደሮች ካሉ የያዙትን መሬት ተቀምተው በመንግስት የተጠየቁትን ክፍያ መክፈል
ለሚችሉ ሰዎች የምናድል መሆናችንን እወቁ በማለት የስርዓቱ ባለስልጣናት ሰኔ 7/2006 ዓ.ም ህዝቡን ሰብስበው ሲያሰፈራሯቸው እንደዋሉ
የደረሰን መረጃ አስትውቋል፣፣
በተሰብሳቢዎች
በኩል የተሰጠ መልስ እናተ የመንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት እንደሚለው መሬት የማይሸጥና የማይለውጥ መሆኑንና የሁሉም
ብሄር ብሄረስቦች መሆኑን ነው የሚያስቀምጠው ይሁን እንጂ እናንተ የመንግስት ባለስልጣን ተብየዎች ግን እንደፈለጋችሁ ስታደርጉት
ነው የምትታዩት አብዛኛው የሃገራችን ህዝብ በመሬት እጦት ምክንያት ወደስደት እያመራ መሆኑን ልታውቁ ይገባል ሲሉ በምሬት አስረድተዋል፣፣
በዞኑ ባለስልጣናት
የቀረበውን ሃሳብ በመቃዎም መሬታችሁን ተረከቡን በማለት ተበሳጭተው መድረኩን ረግጠውት ከወጡት አርሶ አደሮች ለመጥቀስ፣- አቶ ተስፋየ
ገብሩ የማይ ካድራ ነዋሪ፤ ወ/ሮ ማሚት ካህሰ፤ ሃጂ መሃመድ ትኩእና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው ለማወቅ ተችሏል፣፣