Wednesday, June 25, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ ፖሊሶች መሳርያና ቦምብ በመሸጥ ተግባር ላይ እንደተሰማሩ ተገለፀ፣፣



ታህታይ አድያቦ ውስጥ የሚገኙ ፖሊሶች የተሰጣቸው ህዝባዊ ሃላፊነት ወደ ጎን ትተው የህዝቡን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል መንገድ በመሳርያ ንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው እያሉ የሚቆጣጠራቸው አካል በማጣታቸው ምክንያት ሰኔ 9/2006 ዓ/ም ንጋት ላይ ሰሌዳ ቁጥርዋ 0025 በሆነችው የፖሊስ ተሸከርካሪ መሳርያና ጥይት ጭነው ባድመ አካባቢ በሚገኘውና በአቶ ነጋሲ  የእርሻ ቦታ ላይ መሳርያዎቹን በማሽላ ገለባ በመሸፈን ሊሸጡት ወደ ተከዜ አካባቢ ይዘውት እንደሄዱ የአይን ምስክሮች አስታወቁ፣፣
     የአይን እማኞች እንደገለፁት ህጋዊ ያልሆነውን መሳርያዎች በማመላለስ ስራ ላይ ተሰማርታ የነበረችውና ዘነበ በተባለው ሾፌር ተይዛ የነበረችው የመንግስት ተሽከርካሪ ከበላይ የፖሊስ አመራሮች ጋር በመተባበር ይህን መስል አስነዋሪ ተግባር መፈፀማቸውና የአገሪቱን ፀጥታ እያስከበርን ነን በሚሉ በእንደዚህ አይነት እስነዋሪ ድርጊት መሰማራታቸው ቅንጣት ያህል ላገር ደህነነት እንደማያስቡ ማረጋገጥ ይቻላላ ሲሉ አስረድተዋል፣፣
      ከፍተኛ ወንጀል እየፈፀሙ የሚገኙ ከላይ እስከታች የሚገኙ ባልሰልጣናት መሆናቸውና ህዝቡም የተደራጀው የስርቆት መረቡ ለማጋለጥ ቢፈልግም በኋላ የሚመጣውን ችግር በማወቁና ስጋት ላይ በመውደቁ ምክንያት ሁኔታውን ከመግለፅ እንደተቖጠበ ለማወቅ ተችለዋል፣፣