Saturday, June 28, 2014

በአዲግራት ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ ፖሊስ አባላት በህዝብ ላይ በሚያደርሱት ግፍ የተበሳጩ ወገኖች የመግደል እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸው ታወቀ፣፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በላይ ገብረ የተባለውና ትውልድ ሃገሩ ቀርሰበር አከባቢ የሆነው የወያኔ ኢህአደግ ፖሊስ አባል አዲግራት ከተማ  ባልታወቀ መንገድ ሰኔ 14 / 2006 ዓ/ም በጥይት ተገድሎ እንደተገኘ ለማወቅ ተችለዋል፣፣
      መረጃው ጨምሮ በአዲግራት ከተማ የሚገኙ የፖሊስ አባላት በተደጋጋሚ ህዝብን እንደሚያገላቱ በጉቦና አድልዎ የተበላሹ በመሆናቸው ምክንያት መላው የከተማው ህብረተሰብ ምሬቱን እያሰማ መቆየቱንና በኋላም ፖሊሱ በከተማው ማህል ተግድሎ ሬሳው ተጥሎ መገኘቱ የህዝብ ምሬት መገለጫ መሆኑን የተረዱ ፖሊሶች ተመሳሳይ እጣ በነሱም ላይ እንዳይደርስ በስጋት ላይ እንዳሉ አስረድተዋል፣፣
       ባለፈው ግንቦት 5/ 2006 ዓ/ም የሑመራ ከተማ ወጣቶች የከተማዋ ፖሊስ አባል ለሆነው ደብድበው ጉዳት ስለ አደረሱለት ሆስፒታል ውስጥ ገብቶ እየታከመ መሆኑን ባለፈው የዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል፣፣