በደረሰን መረጃ መሰረት
ከኦሮሚያ ክልል እየተፈናቀሉ ያሉ የትግራይና የአማራ ተወላጅ የሆኑ ዜጎች በ1977 ዓ/ም በደርግ ስርዓት በሰፈራ ስም ወደ ኢሊባቡርና
ጂማ የተወሰዱ ሲሆኑ በህጋዊ መንገድ መሬት ተሰጥተው ለ29 ዓመታት ኑሮ መስርተው የቆዩና፣ በአሁኑ ጊዜ አስተዳዳሪዎቹና ግለሰቦቹ
የአካባቢውን ተወላጆች መሬታችንን ልቀቁልን በሏቸው እያሉ በማነሳሳት ከ3 ሺህ በላይ ዜጎቻችን ያለምንም ዋስትና አፈናቅለው እያባረርዋቸው
እንደሆነ መረጃው አስረድቷል፣፣
እኒህ የትግራይና የአማራ ተወላጅ የሆኑ ተፈናቃዮች በአካባቢው አስተዳዳሪ
መሬታችንን ልቀቁልን ሲባሉ ህጋዊ መሬታችንን አንለቅም ያሉትን በዱላ እየቀጠቀጡ በማሰር ወደ ትውልድ ቦታቸው እየመለሷቸው መሆኑን
ያገኘነው መረጃ ጨምሮ አመልክቷል፣፣
ይህ በዜጎች መካከል ተፈጥሮ ያለው ጥላቻና አለመግባባት ገዥው የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
መንግስት ሆን ብሎ የፈጠረው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ነው ሲሉ በርካታ ወገኖች በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፣፣