በመረጃው መሰረት በከናማ
ወረዳ የሚኖረው ህዝብ እያሰማው ካለው ጥያቄ ውስጥ በአካባቢያችን እየተሰራ ባለው መንገድ ስራ ላይ በመጀመሪያ የስራ እድሉ ለኛ
መሰጠት ሲገባው ከለላ ክልል ለመጡ ዜጎች መሰጠቱ ተገቢነት እንደሌለውና እኒህ ዜጎችም በአስቸኳይ ከክልላችን
መውጣት አለባቸው በማለት ከባድ ተቃውሞ እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ፣፣
የአፋር ክልል ተወላጆች ከለላ ክልል ተወላጅ በመንገድ ስራ የተሰማሩ የቀን
ሰራተኞች ላይ ያነሱት የተቃውሞ ውጤት መንስኤው ከፋፋዩ የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ያቀነባበረው
ሲሆን የከናማ ነዋሪ ህዝብና የወረዳው ሚሊሻዎች በአንድ ላይ ተባብረው በአካባቢው የሚያቋርጠውን መንገድ በመዝጋታቸው የትራፊክ እንቅስቃሴ
ይሁን እግረኛ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ስራ ሊሰራ እንዳልቻለ ሊታወቅ ተችሏል፣፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልላችን በሚሰራው መንገድ የስራ ዕድል በቀዳሚነት ለክልሉ ተወላጆች ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ወደ ሚመለከተው አካል አቤቱታ
ቢያቀርቡም ሰሚ አካል በማጣታቸው ምክንያት በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፣፣