Friday, June 27, 2014

መቐለ ከተማ በሚገኙ ድርጅቶች ተቀጥረው ሚሰሩ ዘበኞች ህጋዊ ባልሆነ ስራ በተሰማሩ የሰራዊት አዛዦች እየተገደሉ መሆናቸው ምንጮቻችን ከከተማው ገለፁ፣፣



በደረን መረጃ መሰረት በመቐለ ከተማ በሚገኘው የህዝብ መናሃሪያ በዘበኝነት ተቀጥሮ ሲሰራ የነበሩ አቶ ተ/ወይኒ የተባለ ግለ ሰብ ሻንበል ሃይለ ሃይለ(ዓንቂ በሚል ቅጥያ የሚታወቅ የሰራዊት አባል አንዳንድ ስለ መናሃሪያው ጥያቄ በመጠየቀበት ጊዜ ለምን ትጠይቀኛለህ በማለት በተፈጠረ ግጭት በታጠቀው መኣሪያ ተኩሶ እንደገደለው ታወቀ።

    ይህ የመከላከያ ሰራዊት አባል የሆነ አዛዥ በመግደሉ ለግዜው የታሰረ እንኳን ቢሆን የበላይ አዛዦቹ ከአስረዉት ከነበሩ ፖሊሶች በመግባባት ጉዳዩ ሳይጣራ ወድያዉኑ አውጥተው የወሰዱት ሲሆኑ የሞተው ግለሰብ ቤተሰብ የሆኑት የወድማችን ገዳይ የት አለ ብለው በጠየቁበት ግዜም አሉታዊ መልስ በመስጠት ለሁለተኛ ግዜ ጥያቄ እንዳይጠይቁ አስፈራርተው እንዳባርርዋቸው መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል፣፣