Saturday, June 28, 2014

የትግራይ ምእራባዊ ዞን ነዋሪዎች ከመንግስት ጎን ታጥቃችሁ መቆም አለባችሁ እየተባሉ በወያኔ ኢህአዴግ መንግስት እየተገደዱ መሆናቸውን ምንጮቻቸን ከቦታው ገለፁ፣፣



በመረጃው መሰረት የትግራይ ምእራባዊ ዞን ነዋሪዎች ነጋ ጠባ መሳርያ ታጥቃችሁ ከመንግስት ጎን መሰለፍ ይኖርባችኋል እየተባሉና ይህንንም በማስመልከት ስብሰባ ላይ ተጠምደው ስለሚውሉ እለታዊ ኑሮአቸውን መምራት ስላልቻሉ በስርአቱ ላይ ምሬታቸው እየገለፁ እንደሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣፣
    በተለይ በሁመራ ከተማ “ታገሉ“ የሚል ምልክት በተለያዩ መንገዶችና ቀበሌዎች መለጠፉንና ነዋሪ ህዝቡም አንታገልም የሚል መልስ በመስጠቱ ምክንያት ስጋት ላይ የገቡ የስርአቱ ካድሬዎችና አስተዳዳሪዎች ለከተማው ነዋሪ ህዝብ ነጋ ጠባ ወደ ስብሰባ እንዲወጣ በማስገደድና በማስፈራራት ስራ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ መረጃው አስታውቀዋል፣፣
    የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች በወያኔ ኢህአዴግ ካድሬዎች እየተፈፀመባቸው ያለው የማስፈራራት ዛቻ ሳይበግራቸው በግድ ታገሉ ለሚለው የስርአቱ መመርያ እንዳልተቀበሉት የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣፣