Saturday, June 28, 2014

በአዲስ አበባ ውስጥ የካ ክፍለ ከተማ አዋርያ በተባለው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች በወያኔ ኢህእዴግ ስርአት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በወጡበት ሰአት በፌደራል ፖሊስና በአግአዚ ኮማንዶዎች እንዲበተኑ መደረጉ ተገለፀ፣፣



የአካባቢው ነዋሪዎች በስርአቱ እየወረደባቸው ያለው ግፍና በላያቸው ላይ እያጋጠመ ያለውን ማህበራዊ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኙለት ብለው ሰኔ 14/ 2006 ዓ/ም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በወጡበት ሰአት በድርጊቱ ስጋት ላይ የገቡ የከተማዋ ባለስልጣናት ፌደራል ፖሊስና የአግአዚ ኮማንዶዎችን  በማሰማራት ወደ ተቃውሞ ለወጣው ነዋሪ በዱላ እየደበደቡና በላዩ ላይ ግፍ እየፈጸሙ ሰልፈኛውን እንደበተኑት ለማወቅ ተችለዋል፣፣
     በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት ህዝቡ በመንግስት ላይ ተቃውሞና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ይችላል የሚል ድንጋጌ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆንም የስርአቱ ባለስልጣናት ግን ህገ መንግስቱን ለራሳቸው በሚጥም መንገድ በመተርጎም በደል ተፈፀመብኝ ብሎ በተረጋጋ ሁኔታ ብሶቱን በሰላማዊ መንገድ ለመግለፅ ሰልፍ ለሚወጣ ህዝብ በተደጋጋሚ በመሳርያ ሃይል እንደሚበትኑት ይታወቃል፣፣