እነዚህ በትግራይ ክልል እንደርታ ወረዳ ዙርያ ኲሓና አካባቢዋ የሚኖሩ ዜጎቻችን በተለይ እስከ ሰኔ
11 /2006 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በአስተዳዳሪዎችና በታጣቂዎች እየተገደዱ ወደ ስብሰባ በሃይል ይወጡ እንደነበሩ መረጃው የገለፀ
ሲሆን በዚህ የተነሳም ነዋሪዎቹ እለታዊ ስራችንን እንዳንሰራና ኑሮአችንን በተገቢው መንገድ እንዳንመራ ስርዓቱ እንቅፋት እየሆነብን ነው በማለት የተሰማቸውን ስሜት እየገለፁ እንደሚገኙ
የተገኘው መረጃ ገለፀ፣፣
መረጃው በማስከተል የስብሰባው አጀንዳ። የ2006 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም
እንዴት እንዳለፈና ቀጣይ 2007 ዓ,ም ለሚደረገው ምርጫ በምን መልክ
እንዘጋጅበት የሚልና ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ እድሜው አቅመ አዳም ከደረሰ የህወሃት አባል መሆን እንዳለበትና የስራ እድልም እንደሚከፈትለት
የሚሉና ሌሎችንም ያካተተ አጀንዳ እንደሆነ ቢገለፅም ህዝቡ ግን በአስተዳዳሪዎች የቀረበውን ሃሳብ እንዳልተቀበለውና ተቃውሞውን እንዳሰማ
መረጃው አክሎ አስታውቀዋል፣፣