በምንጮቻችን መረጃ መሰረት
ሰኔ 11/2006 ዓ.ም በማይ ካድራ ከተማ የቃፍታ ሁመራ ምክትል አስተዳዳሪ ወ/ሮ የሺ የተባለች የስርዓቱ ካድሬ ከህዝቡ ጋር ሳትረዳዳ
አግባብነት በሌለው መንገድ መሬት እየለካች በነበረችበት ጊዜ አንድ የሰማእት እናት የሆኑ ወ/ሮ አብረሀት የተባሉ እማ ወራ መሬቴን
አትለኪ የኔ መሬት ድንበሩ የታወቀ ነው ተይ ብሎ ስለተናገርዋት ብቻ እጇቸውን መታ እንደሰበረወችቻቸው ለማወቅ ተችሏል፣፣
መረጃው ጨምሮ
ይህቺ ተበዳይ እናት የህክምና ማስረጃ በመያዝ በዚህች ግፈኛ አስተዳዳሪ ክስ ለመመስረት ወደ ሚመለከታቸው አካልት በሄድበት ጊዜ
የስርዓቱ ተላላኪ የሆነው አቃቢ ህግ ደግሞ ክስ አንቀበልም ከፈለግሽ መታረቅ ትችያለሽ በማለት የመክሰስ መብትውን በመክልከል የባልስልጣኗን
አስነዋሪ ተግባር እንዳይጋለጥ እንደተከላከለላት ታውቋል፣፣
በተመሳሳይ
ዜና በአደባይ ከተማ የአደባይ ከተማ የፀጥታ ሓላፊ ገብረማርያም የተባለ ካድሬ መሬት እየከፋፈለ በነበረበት ሰዓት አንዳንድ ነዋሪዎች
በማታውቀው ገብተህ መሬት አትለካ ሲሉት ባለመስማቱ የተነሳ አንድ ሙሉጌታ የተባለ መሬቱ የተለካበት ተበዳይ ወገን ለፀጥታ ሃልፊው
በዱላ እንደደበደበውና በሆስፒታል ገብቶ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ
አስረድቷል፣፣