Monday, June 23, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን መደባይ ዛና ወረዳ ሰለኽለኻ ከተማ የሚገኙ የፖሊስ ትራፊክ ለሾፌሮች መንጃ ፍቃዳቸው እየቀሙ ጉቦ እያስከፈሉዋቸው መሆናቸው ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣፣



በመደባይ ዛና ወረዳ ሰለኽለኻ ከተማ የሚገኙ ፖሊስ ትራፊክ በመስመሩ የሚንቀሳቀሱ ሾፌሮች የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው ከህግ ውጪ መንጃ ፍቃዳቸው እየቀሙ ጉቦ እንዲከፍሉ እያስገደዱዋቸው መሆኑንና አንከፍልም ላሉትም የፈፀሙት ጥፋት ሳይኖራቸው መንጃ ፍቃዳቸው ቀምተው በመክሰስ እየቀጡዋቸው መሆናቸው ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
     በህዝቡ ላይ ችግር እየፈፀሙ ካሉ የሰለኽለኻ ፖሊስ ትራፊክ አባላት አንዱ ዋና ሳጅን ሃደራ አብርሃ የተባለው ሲሆን ሰኔ 4 /2006 ዓ/ም  እኬሌ ቤት ሄደህ 500 እቁብ ክፈልልኝ አልከፍልም ካልክ እቀጣሃሎህ እያለ እያስፈራራቸው እንደሆነ ከሽፎሮቹ የተገኘ መረጃ አስረድተዋል፣፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ በአከባቢው የሚገኙ የፖሊስ ትራፊክ በሙስና የተዘፈቁ በመሆናቸው ምክንያት ቀጣይ ጉቦ ለመክፈል የተሸገሩ የተሽከርካሪ ሾፌሮች ሰርተን ያገኘነው ገቢ ሁሉ ግዜ ለትራፊክ ፖሊስ በመክፈላችን ምክንያት ችግር ላይ ወድቀናል የሚከታተል የመንግስት አካልም አጥተናል በማለት ብሶታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሆኑ መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል፣፣