Monday, June 23, 2014

በትግራይ ማእከላዊ ዞን ላዕላይ ማይጨው ወረዳ ከስደት የተመለሱ ወጣቶች ሰርተው ሊመልሱት የተበደሩትን ገንዘብ ከፍተኛ ወለድ ክፈሉ ስለተባሉ ምሬታቸዉን እየገለፁ መሆናቸውን ታወቀ፣፣



እነዚህ ከ150 በላይ የሚሆኑ ከስደት የተመለሱ የላዕላይ ማይ ጨው ወረዳ ነዋሪዎች በስርዓቱ ካድሬዎች ተደራጅተው ሰኔ 10 2006 ዓ/ም ከማረት በብድር እንዲወስዱ ቢደረግም በኋላ         ለተበደሩት ገንዘብ 15 ከመቶ ወለድ እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ለኪሳራ እንደተጋለጡና በስርኣቱ ላይ ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
    እነዚህ ከስደት ተመላሾች “ መንግስት የገባልን ቃል ሊተገብረው አልቻለም። ምክንያቱ ከንግድ ባንክ የተበደረ 5 ከመቶ ወለድ ሲከፍል እኛ ከማረት የተበደርን ግን 15 ከመቶ ወለድ እንድንከፍል ተገደናል ሲሉ ከገለፁ በኋላ መንግስት ለኛ ሊያቛቁም ሳይሆን አሳቢ መስሎ በመቕረብ እየነገደብን ነው አገራችን ለቀን መሄድ ይሻለናል” በማለት ዳግም ወደ ስደት እየጠፉ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣