Tuesday, August 5, 2014

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ከ15 ወረዳዎች የተወጣጡ ከረዳት ኢንስፔክተር በላይ ማዕረግ ያላቻው የፖሊስ አባላት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘለቀ መሬነት አስቸኳይ ስብሰባ መጠራታቸው ተገለጸ።



በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ ከዞኑ 13 የገጠር ወረዳዎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ከረዳት ኢንስፔክተር በላይ ማዕረግ ለሚገኙ የፖሊስ አባላት በተደረገላቸው አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ከሃምሌ 23 እስከ 25 / 2006 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ቀናት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘለቀ መሪነት እንደተካሄደ የደረሰን መረጃ አስረድተዋል።
     የተካሄደው ስብሰባ አጀንዳም በግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መያዝን ተከትሎ ህዝቡ አመፅ ሊቀሰቅስ ይችላል ስለዚህ እንዴት መያዝ እንዳለበት የሚጠቁም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንድሆነና ከተሰብሳቢዎችም አመፁንስ ልናስቆመው እንችላለን እየጠፋ የሚሄደው የሰው ሃይል ግን እንዴት ልናስቆመው እንችላለን ሲሉ ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ እንዳላገኙለትም ምንጮች ከቦታው አክለው አስረድተዋል።