በምንጮቻችን መረጃ መሰረት ይህንን ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር ከተለያዩ
የሃገራችን አካባቢዎች ወደ ገዳሙ ለመጡ አማኞች አይዟችሁ ከጎናችሁ
አለን የሚልና ለስርዓቱ ካድሬዎች ደግሞ ማስጠንቀቂያ የያዘ ፓምፕሌትና መፅሄት ብስራት መበተኑንና መበተኑን ያስተዋሉ የፖሊስ አዛዦችም
በከባድ ጭንቀት ስለወደቁ ለበታች አባሎቻቸው የተበተነውን ወረቀት ቶሎ ብለው እንዲሰበስቡት ትዕዛዝ በመስጠት ከቦታው እንደተሰወሩ
ያይን እማኞችን መሰረት ያደገው መረጃ አስረድቷል።
ከዚህ በተያያዘ የዕጉብ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ገብረአብዕዝጊ ከምክትሉ ተስፋሁነይ መሰለ ጋር በመሆን ህዝቡን ሰብስበው ትህዴን በውስጣችን ገብተው
ስለሆነ እነሱን ለመተባበር የተሰማራ ሰው አለ ይህንን ደግሞ ማውጣት አለብን በማለት ህዝቡን ሲያስፈራሩት እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል።