ካካባቢው በተገኘው መረጃ
መሰረት በበራህሌ ወረዳ፤ ሳባ በተባለው ቀበሌ የሚገኙ የ 21ኛ ክፍለጦር ወተሃደሮች ሃምሌ 21/2006 ዓ/ም
በራህሌ ወረዳ በሚገኘው ሰላማዊ ህዝብ ላይ ግፍ መፈፀም በጀመሩበት ወቅት ህዝቡ የበቀል እርምጃ እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል፣፣
በደል የደረሰበት ህዝቡ በወታደሮቹ የበቀል እርምጃ በወሰደበት ግዜ
የ8ኛ ሻለቃ 2ኛ ሃይል ምክትል አዛዥ የነበረውን መቶ አለቃ ገብሩ የተባለውን በከባድ ተደብድቦ
ለህክምና ወደ መቐለ እንደተወሰደ የገለጸው መረጃው ከሲብሉ ማህበረሰብም ዓብደልወሃብ ወይም ወዲ ሻምበል በሚል የሚጠራውን ግለሰብ
በወታደሮቹ ክፉኛ ተደብድቦ መቐለ ከተማ ውስጥ በህክምና እንደሚገኘ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣