Saturday, August 9, 2014

በርከት ያሉ ወጣቶች ለወያኔ ኢህአዴግ ስርአት በመቃወም ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ተቀላቀሉ።



በዚህ ሳምንት ወደ ድርጅቱ ከተቀላቀሉት ወጣቶች የተወሰኑትን ለመግለፅ
-     ኪሮስ ተወልደ ብርሃን ከማእከላዊ ዞን፤ አህፈሮም ወረዳ፤ ማይ ሃማቶ ቀበሌ
-     ዓወት ገብረማርያም ገብረኪዳን። ከማእከላዊ ዞን፤ አሕፈሮም ወረዳ ደጎዝ ቀበሌ
-     ኤፍሬም ለአከ ወሉ ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ራማ ቀበሌ
-     አላይ ተኹሉ ቦራ፤ ፍሻለ በይን ገብረህላሴ፤  ገብረሂወት ሀይለ ገብረና አብርሃለይ ታደሰ ተስፉ ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያዎ ወረዳ፤ ምድረ ፈላሲ ቀበሌ
-     አለም በሪሁ ገብረየሱስ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን፤ ጉለመከዳ ወረዳ፤ ዓዲ ተስፋ ቀበሌ
-     ቴዲ ፍትዊ በርሀና ገብረስላሴ ፍስሃ ተኽላይ ክትግራይ ማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲ ፍታው ቀበሌ
-     ጉዕሽ በርሀ ገብረሚካኤል ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ምሕቋን ቀበሌ
-     ጉዕሽ አረጋዊ ተኹሉ ከትግራይ ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ሃፍቶም ቀበሌ
-     የማነ አለነ ገብረመስቀል ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ ክልተ ቀበሌ
-     ገዳሙ ንጉሰ ገብርሄት ከትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ማይ ወዲ ዓንበራይ ቀበሌ
-     ኪሮስ ነጋሲ ወልደገብሪኤል ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ አሕፈሮም ወረዳ፤ ሆያ መደብ ጣብያ ሲሆኑ።--
         እነዚህ ወጣቶች ወደ ትህዴን ተቀላቅለው እንዲታገሉ ያስገደዳቸው ምክንያት ሲያብራሩ-- ባሁኑ ግዜ በህብረተሰባችን ውስጥ ሰላም የሚባል ነገር የለም መጪው አመት 2007 በሚደረገው አስመሳይ ምርጫ በተያያዘ ሁኔታም በርካታ ንፁሃን የተቃዋሚዎች ደጋፊ ነህ እየተባለ በግልፅና በድብቅ እየታሰረና እየተንገላታ መሆኑን ገልፀዋል።
         በተለይ ዓወት ገብረማርያም የተባለው ወጣት ቀደም ብለው ከሳውዲ አረብያ ከተመለሱት እንደሆነ መግለፁንና መንግስት ከአውሮፕላን ማረፍያ ካወረደን ዕለት ጀምሮ ወደየ ወረዳቹህ ከሄዳችሁ በኋላ ለስራ ማንቀሳቀሻ የሚሆን ገንዘብ ይሳጣቿሃል ብሎ ቢሸኘንም ወደየ ቦታችን ሄደን ብንጠይቅ ግን በነፃ የሚሰጣቹሁ ገንዘብ የለም ከፈለጋችሁ በደ.አ.ን.ት በብዱን ተደራጅታችሁ ብድር መውሰድ ትችላላችሁ በማለት ስርአቱ የገባላቸውን ቃል መተግበር እንዳልተቻለ  አስታውቀዋል።
        ወጣት ዓወት በበኩሉ ብድር ወስደው ወዳልተፈለገ እዳ እንዲገቡ ስላልፈለጉ ብድር አንፈልግም ብለው በራሳቸው ገንዘብ በአንስተኛ የንግድ ስራ ቢሰማሩም ምክንያት እየፈጠሩ ሊያሰሯቸው ስላልቻሉ በዚሁ ሁኔታ ተማርሮና የችግሩ መፍትሄ ትግል እንደሆነ በማመን ወደትህዴን እንደተቀላቀለ ለመረዳት ተችሏል።