Thursday, August 7, 2014

በጎንደርና በሁመራ አካባቢ የሚገኘው የስልክ መስመር በስርዓቱ ብልሽው አሰራር በመቋረጡ የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ የቀን ስራውንሊያሳልጥ እንዳልቻለ ምንጭዕቻችን አስታወቁ፣፣



   ምንጮቻችን እንደገለፁት የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ባልስልጣናት በትግራይና በአማራ ክልል ድንበር ላይ እየተከተሉት ባለው የመሬት አስተዳደር ለአንዱ ሰጥተህ ለአንዱ በሚከለክሉት አካሄዳቸው የተነሳ የተፈጠረው ግጭት ሳያበርድ የአውደራፊና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ዜጎቻችን ከአንዱ ክልል ወደሌላው ክልል እየወሰዳችሁ አታገላብጡን ከፈለጋችሁ ከመሬታችን ጋር ወደ ሱዳን ስደዱን ሲሉ ለስርዓቱ ባለስልጣናት በመቃወማቸው ምክንያት በአካባቢው የስልክ መስመር እንዲቋረጥና እንዳይሰራእንዳደረጉ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
   ስርዓቱ ወስዶት ባለው የስልክ መስመር መቁረጥ የተነሳ የሁለቱ ክልል ወገኖቻችን ማለት የጎንደራ የሁመራና የአካባቢው የሚኖሩ በንግድ ስራ የሚተዳደሩ ዜጎቻችን ስራቸውን እንዳያሳልጡ ትልቅ እንቅፋት እንድሆናቸው በመግለፅ መንግስት እራሱ በፈጠረው ችግር ለህዝብ መገናኛ ስልኮችን ዘግተህ መቅጣት አግባብነት የለውም በማለት ምሬታቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ የተቸገሩ ወገኖቻችንን መሰረት በማድረግ ምንጭዕቻችን በላኩልን መረጃ ለማወቅ ትችሉል፣፣