Thursday, August 7, 2014

የሰቲት ሁመራ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ለመታውቂያ ካርድ ማውጫ ከመጠን በላይ ገንዘብ እንዲከፍል ስርዓቱ በማስገደዱ ምክንያት ነዋሪዎቹ ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸውን ተገለጸ፣፣



    ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት በሰቲት ሁመራ ከተማ የሚኖር ህዝብ የማንነት ወረቀት ለማውጣት እየተሸገረ መሆኑና ማውጣት የሚችል ከሆነም ከመቶ ብር በላይ እንዲከፍል ስለሚገደድ ለመታውቂያ ይህንን ያሚያክል ገንዘብ አናወጣም ብሎ ለተቃወመም ፀጉረ ለወጥ፤ የትህዴን ተባባሪና መንገድ መሪ ነህ እየተባለ በመታስረ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ትችሏል፣፣
    ከሁመራ ከተማ ሳንወጣ የምግብ ዘይት ዋጋ ከመወደዱ በላይ ጠቅልሎ በመጥፋቱ ምክንያት ህዝቡም በውድ ዋጋ ማግኘት እንዳልቻለና ከባድ ችግር ላይ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው መንስኤውም የህወሃት ኢህአዴግ ስርአት እየተከተለው ባለው ብልሹ አስተዳደራዊ ምክንያት እንደሆነ እየታወቀ የተፈጠረውን ችግር  በነጋዴዎች እያሳበበ መሆኑንና በዚህም ምክንያት በከተማዋ ለሚገኙ 3ት ነጋዴዎች ህዝቡ እንዲያማርር አድርጋችኋል በማለት እንዳሰራቸው ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ ለመረዳት ተችሏል፣፣