Sunday, August 3, 2014

በሰሜን ሽዋ ዞን መረሃ-ቤቴ ወረዳ አለም ከተማ የነበረውን ትራንስፎርመር በመንግስት ትእዛዝ ሊነሳ በተወሰነበት ሰዓት የአካባቢው ማህበረሰብ ጠንካራ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዱ ተገለፀ፣፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መርሃ ቤቴ ወረዳ አለም ከተማ ውስጥ ከዚህ በፊት ተተክሎ የነበረውን የመብራት ሓይል ትራንስፎርመር ምክንያቱ ባልታወቀ የክልሉ መንግስት ከአካባቢው እንዲነሳ ትዕዛዝ ስላወረደ የመብራት ሓይል ሰራተኞችና ፖሊስ አንድ ላይ በመሆን ንበረቱን ነቅለው ‘ለመውሰደ በሞከሩበት ሰዓት የአለም ‘ከተማ ማህበረሰብ ጠንቃራ የሆነ ተቃውሞ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል፣፣
   መንግስት ከአለም ከተማ ላይ እያነሳው ላለው የመብራት ሓይል ትርንስፎርመር ለምን እንደሚያነሰው ከአካባቢው ማህበርሰብ ጋር ሳይመካከርና ምንም አይነት ማስረጃ ሳይሰጥ ለመውሰድ መሞከሩ ስርዓቱ ምን ያክል ከህዝብ ተነጥሎ እንዳለና በህዝብ ላይ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው ሲል የገለፀው መረጃው በዚህም የተነሳ የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ በአንድ ድምፅ ተቃውሞ በማካሄዱ ለተተከለው ትራንስፎርመር ነቅለው ለመውሰድ ከመጡት የስርዓቱ ተላላኪ በሆኑት ካድሬዎችና በህዝቡ መካከል ግጭት ስለተፈጠረ በስርዓቱ በኩል የነበረው ትራንስፎርመሩን የመንቀል እኩይ ተግባር በህዝብ ተቃውሞ የቆመ ሲሆን ህዝቡ በበኩሉ መንግስት እየወሰድ ያለውን ፍትሓዊነት የሌለው እርምጃ በማውገዝ የተሰማውን ቅሬታ እያሰማ እንደሚገኝ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስታውቋል፣፣