Sunday, August 3, 2014

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ራያ አዘቦ ወረዳ የሚገኙ የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አስተዳዳሪዎች በእስልምና አማኞች መካከል ልዩነት እየፈጠሩ ርስበርሳቸው እያጋጯቸው መሆኑ ታወቀ፣፣



በራያ አዘቦ ወረዳ አላማጣ ከተማ ኩኩፍቶ እንዲሁም  በጥሙጋ እና ዋጃ አካባቢ የሚገኙ የስርዓቱ አስተዳዳሪዎች በወረዳው የሚገኙትን የእስልምና ሃይማኖት አማኞችን አሸባሪ፤ ውሃቢ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሙስሊም መንግስት ለመመስረት የሚጥሩ ናቸው በማለት ሌሎችንም ስሞች  በመስጠት በመካከላቸው ልዩነት በመፍጠር እያጋጯቸው እንደሆኑ ምንጮቻችን ከስፍራው በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል፣፣
    መረጃው ጨምሮም የራያ አዘቦ ወረዳ አስተዳዳሪዎች በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ እየተፈፀሙት ያለው ግፍና ሰቆቃ ከቀን ቀን እየከፋ መሄዱን በመግለፅ በዚህ የተማረሩ የእስልምና ሃይማኖት አማኞች በስርዓቱ ላይ እንዳያምፁ በመስጋት ከሃምሌ 5 /2006 ዓ/ም ጀምሮ እያንዳንዳቸው በማህበራዊ ህይወት ስራ ላይ እንዳይተጋገዙ እንዲሁም በሰርግ፤ በእድርና በዱዓ አብረው እንዳይሰባሰቡ እየከልከሏቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣
    እኒህ በስራዓቱ ግፍ እየተፈፀመባቸው ያሉት የእስልምና አማኞች በበኩላቸው የሃይማኖት ነፃነት ይከበር የሚል ጥያቄ ስላነሳን ብቻ እንደጠላት ተቆጥረን ከህብረተሰባችን ጋር አብርን ማህበራዊ አገልግሎት እንዳናገኝ በአስተዳዳሪዎች ማስፈራራት ተሸማቀን እንገኛለን ሲሉ ከገለፁ በኋላ ለእነዚህ ልዩነት ለሚፈጥሩ የስርዓቱ ተላላኪዎች ደግሞ ለማታለያ የሚሆን የህወሃትንና የኢትዮጵያን ባንዴራ እየሸለሟቸው መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል፣፣