Friday, February 20, 2015

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ የማክሰኘት ከተማ ነዋሪዎች የኢህአዴግን ከፋፋይ ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ምንጮቻቸን ከቦታው አስታወቁ።



    በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል፤ ሰሜን ጎንደር ዞን፤ የማክሰኘት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ጥር 25/ 2007 ዓ/ም የብአዴን ኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም ከባድ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ የገለፀው መረጃው ሰልፈኞቹ እያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች ውስጥም መሬታችንን ተገቢ ባልሆነ መንገድ እየተነጠቅን ነው፤ እኛ የቅማንት ብሄረሰብ አይደለንም፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆኑትን ንፁሃን ዜጎቻችን አሸባሪዎች እየተባሉ እየታሰሩ ነው፤ የኢህአዴግ ካድሬዎች ሆን ብለው ከትግራይ ህዝብ ወንድሞቻችን ጋር ለማለያየት በመሬት ሰበብ እያጣሉን ነው፤ እኛ ግን አሁንም ወንድማችን ከሆነው የትግራይ ህዝብ ጋር አንጣላም የሚሉና ሌሎችም እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ከቀኑ 5፣00 ሰዓት እስከ 8፣00 ሰዓት በተማሪዎች መሪነት የተካሄደ ሲሆን ከ 600 በላይ የሚሆን ህዝብ እንደተሳተፈና የገዢው ስርዓት የፖሊስ አባላት ሰላማዊ ሰልፉን ለመበተን አቅም ስላጡ ዝምታ መምረጣቸውን የገለፀው መረጃው በተካሄደው ሰልፍ የተቆጡ የበላይ አመራሮች ሰልፉ የተካሄደው በተቃዋሚዎች አቀናባባሪነት ነው እያሉ ሰዎችን ለማሰር ምክንያት እየፈጠሩ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።