Wednesday, May 6, 2015

የኦሮሞ ህዝብ እያካሄደው ባለው ተቃውሞ ስጋት ውስጥ የገቡት የኦህዴድ/ኢህአዴግ ቡድኖች በደህንነት አባላቶቻቸው አማካኝነት ህብረተሰቡን እያጨናነቁት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።



በደረሰን መረጃ መሰረት በኦሮሚያ ክልል በወለጋ አካባቢ የሚኖረው ህብረተሰብ በኦህዴድ ኢህአዴግ ላይ በተደጋጋሚ ተቃውሞ እያነሳ የሚገኝ ሲሆን በዚ ስጋት ውስጥ የገቡት የክልሉ ባለስልጣኖችም በርካታ ቁጥር ያለው የድህነት አባላት በቦታው በማሰማራት ህብረተሰቡ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ዕለታዊ ስራውን እንዳያሳልጥ የት ነበርህ ወዴት ነህ እያሉ አስረው  እያንገላቱትና  እየገረፉት ቢሆኑም የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ሳይቀሩ ከጭቁኑ ማህበረሰብ ጎን በመወገን በስርዓቱ እየተካሄደ ያለውን እኩይ ተግባር በመቃወም ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል።
   በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ ሚያዚያ 14/2007 ዓ.ም የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የፌደራል ፖሊስ በከተማው በማሰማራት ምንም ወንጀል ያልሰሩ ንፁሃን ወገኖቻችን ቀስቃሽ እየተባሉ በሌሊት እየታፈኑ በመወሰድ ላይ እንደሚገኙና ይህም መጭው ግንቦት ወር 16/2007ዓ.ም በሚካሄደው አስመሳይ ምርጫ ህብረተሰቡ በንቃት እንዳይቃወም አስቀድሞ እየተካሄደ ያለ የስርዓቱ ፋሽስታዊ ተግባር መሆኑን ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል።