ባገኘነው መረጃ መሰረት አምባገነኑ የህወሃት
ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት በክርስትናና በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ጣልቃ በመግባት እየተከተለው ያለውን የመከፋፈል አካሄድ
እንዲቆም በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የሆኑ ትላልቅ መሪዎች ከህዝብ ጋር በህብረት በመሆን ሚያዝያ
19 ቀን 2007 ዓ/ም አቤቱታቸውን ለሚመለከተው የክልሉ አካል እንዳቀረቡ
ታውቋል።
ከነሱት አቤቱታ በከፊሉ ለመግለፅ ያህል ህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከቀደም
ጀምሮ በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ ርካሽ የፖለቲካዊ ጥቅም ሲያገኝበት የቆየ ሲሆን ዛሬም እየተከባበረ የመጣውን የእስልምናና የክርስትና
ሃይማኖት ተከታይ ህዝብ በመካከሉ እየገባ በጥርጣሬ አይን እንዲታይ የሚያደርገው ብልሹ አካሄድ በአስቸኳይ መቆም አለበት የሚል መሆኑን
ለማወቅ ተችሏል።