ከመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አዋቂዎች የደረሰን
መረጃ እንዳመለከተው- ወታደሮቹ መሳሪያቸውን ሽጠው በመጥፋት ላይ እንዳሉ ከገለፀ በኃላ ከሰራዊቱ መካከል አንዱ አምሳ አለቃ ዘላለም
ዘለቀ የራሱንና የጓደኛውን ክላሽ በ45ሺ ብር ሽጦ ሊጠፋ ሲል በባህር ዳር ከተማ እንደተያዘ ለማወቅ ተችሏል።
አምሳ አለቃ
ዘላአለም ዘለቀ በ1992 ዓ/ም ወደ ውትድርና የተሰለፈ ሲሆን የኢህአዴግ ወታደራዊ አመራሮች ባልዋለበት ወንጀል ተንኮል በመሸረብ
እስከ አሁን ድረስ በተደጋጋሚ እያሰሩት ቆይተው ጥቅምት 4/ 2007 ዓ/ም ከእስር ከተፈታ በኃላ ግን በጥርጣሬ አይን መከታተል
ስላበዙበት ክላሽ ሽጦ ሊጠፋ ሲሞክር ተይዞ መኮድ በተባለው ቦታ ታስሮ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።