የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በአማራ ክልል
ጎንደር አካባቢ ልዩ ስሙ ደምቢያ በተባለው ቦታ ለሚኖር ህብረተሰብ የስርአቱ ካድሬዎች ለሁለት ቀናት ያህል የአስገዳጅ ስብሰባ እንዳደረጉላቸው
የገለፀው መረጃው ወጣቶች ትጥቅ ትግል ወደ ሚያካሂዱ ድርጅቶች በመሄድ ላይ ናቸው የሚል ግምገማ ስላላቸው እያንዳንዱ
አርሶ አደር በማስነሳት ልጅህ የት አለ? በማለት እያስፈራሩት እንዳሉና ለቀጣይም ማነኛውም ልጅ ወዴት እንደሄደ ቤተሰቡ ካላወቀ
በላዩ ላይ እርምጃ ይወሰድበታል እያሉ እያስፈራርዋቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ-የአካባቢው ተወላጅ በስራ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ
ሲንቀሳቀስ የቀበሌው አስተዳደር አሳውቆ መሄድ ይገባዋል የሚል ትእዛዝ እንዳወረዱላቸውንና ይህን በተግባር ላይ ለማዋልም እያሰፈረሙት እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያስረዳል።